“ፕሮቴስታንቱን ምን ነካው?”

ከጥቂት ወራት በፊት በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ህብረትና በመሰረት ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሐሰተኛና አስጸያፊ ተብለው መግለጫ የተሰጠባቸው አዳዲስ አገልጋዮችና አገልግሎቶች እስካሁን ድረስ በስፋት እያነጋገሩ ይገኛሉ። ዶ/ር ወዳጄነህ ሰሞኑን በኤክሶደስ ሾው ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ምክንያት ይኸው የ“ሐሰተኛ ነብያት” ጉዳይ ትኩስ ትኩረት አግኝቷል። በዚህ ጽሁፍ “ሰው የሚዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል” የሚለውን መጽሃፍ ቅዱሳዊ ህግ መሰረት አድርጌ የዚህን እያነጋገረ ያለ ችግር መንስኤና መፍትሔ ለመመርመር እሞክራለሁ። ዶ/ር ወዳጄነህ ላነሱት “ፕሮቴስታንቱን ምን ነካው?” ላሉት ጥያቄም መልስ አፈላልጋለሁ።

ሰው መንፈስ ነው? መጽሐፍ ምን ይላል?

መግቢያ  በዚህ ዙሪያ የግሌን አስተያየት ብሰጥ ጥሩ ነው ብየ ያሰብኩት በሐዋርያ ብስራት ብዙአየን (ጃፒ) የተሰጡትን “ሰው ምንድን ነው” ተከታታይ ትምህርቶች በዩቲዩብ ካየሁ በኋላ ነው። ይህን ጽሁፍ ከማንበብ በፊት “ሰው ማን ነው?” ክፍል 1 ትምህርትን መመልከት ንባቡን ቀላልና ፍሬያማ ያደርገዋል። “ሰው መንፈስ ነው፣ ነፍስ አለው በስጋ ውስጥ ይኖራል” የሚለውን ትምህርት ጌታን ከተቀበልኩ ጥቂት ዓመታት በኋላ ተምሬ…

አማላጅ ማነው? ኢየሱስ አዳኝ ወይስ አማላጅ?

በ ፕሮቴስታንት (”ጴንጤ”) እና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነቶች መካከል እንደዋና ልዩነት ከሚታዩት አንዱ አማላጅ ማነው ለሚለው ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ ነው። ፕሮቴስታንቶች ክርስቶስ ነው ሲሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ደግሞ ቅድስት ማርያም ናት ይላሉ፣ አያይዘውም እንዴት አምላክ ራሱ ተማላጅ ደግሞም አማላጅ ይሆናል ይላሉ። ይህ ሁሌም የሚያወዛግብ ሁሉም የሚያውቀው ልዩነታችን ይሁን እንጂ በአማላጅነት ዙሪያ የፕሮቴስታንቱ አመለካከት በእርግጥ ምን…

Why this blog?

I would like to use this first blog post to explain the reason that got me into creating this blog site. I'm generally interested in discussions and even debates that involve religion but never thought of having a blogging site dedicated just for that purpose until very recently. But what I observed the past couple…